ማውጫ ማውጫ

ማስታወቂያ ማስታወቂያ

 

                         ማስታወቂያ

ጉዳዩ፡-የ2014 በጀት አመት የግዥ ፍላጎት ዕቅድን ይመለከታል፤

የፌደራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አወጅ ቁጥር 649/2001 አንቀጽ 8/መ እና አዋጁን ለማስፈፀም ሰኔ 2002 በወጣዉ  መመሪያ አንቀጽ 6/1 መሰረት የቀጣዩን በጀት አመት የግዥ ፍላጎት ዕቅድ አዘጋጅቶ በሚመለከታቸዉ አካላት ማጸደቅና በበጀት አመቱ ጨረታዎችን አስቀድሞ በማዉጣት ግዥ ለመፈፀም የስራ ክፍሎችን የግዥ ፍላጎት ማሰባሰብ አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ይደነግጋል፡፡

ስለሆነም ለመጪዉ የ2014 በጀት ዓመት ለመማር መስተማር፤ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፤እንዲሁም ለአስተዳደር ስራዎች የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ከተሟል የዕቃዎች/አገልግሎቶች ፍላጎት ዝርዝር መገለጫ(Goods standard Specification) ጋር ደረጃቸውን ከጠበቁ፣ ግልጽነትና ወቅታዊነት ካላቸዉ ሰፔስፊኬሽን ጋር እንዲሁም የስራ ክፍሎች የተመደበላቸዉን በጀት መሰረት በማድረግ በየስራ ክፍሎች ዕቅዱ ተዘጋጅቶ በተዘረጋዉ  የኤሌክትሮኒክ የግዥ አስተዳደር ስርዓት (BDU-ePMS) መረጃ ቋት ዉስጥ መግባት እንዳለበት ታምኖበታል፡፡ በዚህም መሰረት  የስራ ክፍሎች ከእቅድ ዉጭ የሚመጣ የግዥ ፍላጎት ጥያቄ እንደማይስተናገድ ከወዲሁ አዉቀዉ ወደ ሲስተም እየገቡ እቅዳቸዉን እንዲያስገቡ መደረግ ይኖርበታል።

ከመረጃ ቋት ያላገኟቸዉንና የግድ እንዲገዙላቸዉ የሚፈልጓቸዉን ዕቃዎች/አገልግሎቶች ስፔስፊኬሽን ወደ ሲስተሙ እንዲገቡላቸዉ በማድረግ የክፍልችሁን የግዥ ፍላጎት ዕቅድ በhttp://10.163.12.12 ወይም http://pms.bdu.edu.et ላይ የሚገኘዉን የሲስተሙን የእቅድ ሞጁል በመጠቀም  እስከ 01/11/2013 ዓ.ም እቅዱን አጠናቅቃችሁ በሲስተሙ እንድታስገቡ እየገለጽን በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ  የግዥ ፍላጎት /እቅድ/ ጥያቄ ሳይቀርብ ቀርቶ ከተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉጪ ለሚቀርብ የግዥ ጥያቄ ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናገድ መሆኑን ከወዲሁ እንድታዉቁት እያሳሰብን የየግቢ ግዥ ክፍሎችም በተሰጠዉ የግዜ ገደብ ዉስጥ በግቢያችሁ የሚገኙ የስራ ክፍሎች እቅዳቸዉን በሲስተሙ አስገብተዉ እንዲያጠናቅቁ ጥብቅ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንድታስፈጽሙ እየገለጽን ከሲስተሙ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለሚያስፈልጋችሁ ማንኛዉም የቴክኒክ እገዛ በሲስተሙ ዋና ገጽ ላይ የሚገኘዉን የባለሙያዎች ስምና የስልክ አድራሻ በመጠቀም መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

                                                   

                                                           የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ማሳሰቢያ፡ -

BiT;EiTEX እና ሕክምና ኮሌጅ የራሳቸውን የጊዜ ሰሌዳ ማውጣትና መልዕክቱን በውስጥ ማስታወቂያ ለተገልጋዮች ማሳውቅ ይችላሉ::

የገፅ ይዘት የገፅ ይዘት

የሲስተም አጠቃቀምን በተመለከተ ቴክኒካዊ እገዛ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተመላከተው ሰንጠረዥ መሰረት ለሚመለከተው ግቢ የተመደበውን ባለሙያ ያግኙ።

No

Expert Name

Email

Phone no

Campus

1.     

 ጎጃም አስጨናቂ

  gojjam121@gmail.com

 0920521136

ጥበብ ሕንፃ ግቢ

2.     

  ሙሴ አየ

  aye.musie@gmail.com     

  0927688782

  ዘንዘልማ ግቢ

3.     

  ማህሌት ገዛኸኝ

  mahletgezahegn@gmail.com

  0918704593

  ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢ

4.     

  አስማማው ጌታነህ

  asmamaw2015@gmail.com

  0918200179

  ጊሽ አባይ /ይባብ/ ግቢ

5.     

 ማርየ የኔአለም

   maryeyenealem@gmail.com

0918457009

  ሳይንስና ማሪታይም ግቢ

6.     

  ዜና ተዘራ    zenawub@yahoo.com 0918761271

  ሰላም ግቢ

7.     

 

   

  ሕክምና ግቢ

8.     

  ሙሉነሽ አለነ

  alenemulunesh@gmail.com

 0924516754

  ዋናው ግቢ

9.     

  ወርቅነሽ ሞገስ

  workneshmoges@yahoo.com

  0921283572

  ቴክኖሎጂ ግቢ

 

ማሳሰቢያ፡-

የሚፈልጉትን ዕቃ በሲስተሙ ያለተመዘገበ ከሆነ እና የዕቃው ዓይነት [የፈርኒቸር፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የኮምፒዩተርና ተዛማጅ እና የፅዳት ዕቃዎች] ከሆነ ለግቢ ለተመደበውን ባለሙያ ኢሜይል እንዲመዘገብሎት ይላኩ።